Photos
Videos
በዛሬው የሕዳር 30 ቀን 2010 ዓ.ም የቅዳሜ ጨዋታ ፕሮግራማችን እነዚህን መሰናዶዎች ይዘን እንጠ...
20
1
ይህ የአንድ ቤቱን ማደስ ያልቻለ ኢትዮጵያዊ ቤት አይደለም፡፡ ይልቁንም የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ጮራ ፈንጣቂው የዘመናዊ ኢትዮጵያ መስራች የአፄ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ የእንጦጦው ቤተ መንግሥት እንጂ ! አስተዳዳሪዋ የእንጦጦ ማርያም ደብር የአቅሜን ሁለት ጊዜ አሳደስኩ ትላለች፡፡ ለከተማዋ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጉዳዩን መላ በልም ብላዋለች፡፡ ባህልና ቱሪዝም ቢሮው ቅርስ የማደስ ስልጣኑ በአዋጅ የእኔ አይደለም ይላል - ወደ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን በመጠቆም፡፡ ቅርስ ጥበቃ በበኩሉ እዚህ ደረጃ መድረሱን የነገረኝ የለም ይላል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው የአርኪዮሎጂ እና የቅርስ አስተዳደር መምህሩ ዶ/ር ተመስገን ቡርቃ “አይደለም ይሄን ያክል ግዙፍ ታሪክ የአባትህ አንዷ ብትር ከጀርባዋ ባለው ማንነት ቅርስ ናት” ይላሉ፡፡ (ምስክር አወል) ዝርዝሩን ያዳምጡ…
81
16
የቅዳሜ ጨዋታ - ሕዳር 9 ቀን 2010
116
13
Posts

አያቶላህ ሆሚኒ፣

የሺአ ሙስሊሞች መሪና የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ መስራች አያቶላህ ሆሚኒ ማን ናቸው ?
እሸቴ አሰፋ በመቆያ መሰናዶው ዘርዘር አድርጎ ይነግረናል…

አያቶላህ ሆሚኒ - Ayatollah Khomeini - መቆያ
youtube.com

አዋጅ ነጋሪው ጋዜጠኛ - አሰፋ ይርጉ…

አሁን ላይ ጋዜጠኛ አሰፋ ይርጉን ስንቶች ያውቁት ይሆን ? ብዙዎች በጆሮ ገብ ድምፁ የሚያውቁት አሰፋ ይርጉ የአብዮቱን ዘመን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና ሌሎች የደርግ ዘመን አዋጆችን በማንበቡ ይታወቃል፡፡ አቶ አሰፋ ይርጉ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትንም በማቋቋሙ ይታወቃል…

መኮንን ወልደአረጋይ በስንክሳር መሰናዶው የእኚህን አንጋፋ ጋዜጠኛ ታሪክ ዳስሷል፡፡...
ወደ ዮትዩብ ቻናላችን ጎራ ብላችሁ እንድታዳምጡ ጋብዘናል…

See More
Assefa Yirgu - አዋጅ ነጋሪው ጋዜጠኛ - አሰፋ ይርጉ - ስንክሳር - በመኮንን ወልደአረጋይ
youtube.com
Posts

የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባው ዶክተር አብይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀመንበር እንዲሁም አቶ ለማ መገርሳን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መረጧል #ShegerWerewoch #Ethiopia

የኦሮሚያ ክልል ሴት የትምህርት ባለሞያዎችን በብዛት በሃላፊነት ቦታ ላይ ልመድብ ነው አለ፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ኤፍሬም ተሰማ እንዳሉት ስምንት መቶ ሠላሣ ሴት የትምህርት ባለሞያዎችን ከየትምህርት ቤቱ ለመመልመል ተጠይቆ አምስት መቶ ሠላሣ አንዱ ተለይተዋል፡፡

እነዚህ አምስት መቶ ሠላሣ አንድ ሴት የትምህርት ባለሞያዎች በሃላፊነት ለመስራት የሚያስችላቸውን ስልጠና ለመከታተል ወደ ወለጋ፣ አምቦ፣ ጅማ፣ ሀሮማያ፣ መዳወላቡና ዲላ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተዋል ብለዋል፡፡

...

ከስልጠናው በኋላ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን እንደሚሆኑ አቶ ኤፍሬም ነግረውናል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በሃላፊነት ቦታ ካሉ ባለሞያዎች የሴቶች ድርሻ እስከ አሁን ከስድስት በመቶ አይበልጥም ተብሏል፡፡

በክልሉ በአጠቃላይ ወደ አስራ ስድስት ሺህ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ አቶ ኤፍሬም ነግረውናል፡፡

ከአስር ሚሊየን በላይ ተማሪዎችና 192 ሺህ መምህራንም በክልሉ አሉ ብለዋል፡፡

(ንጋቱ ረጋሳ)

See More

ህፃናትን በጉዲፈቻ ወደ ውጪ ሀገር ሲልኩ የቆዩ ሰላሣ ዘጠኝ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ዓላማቸውን ካልቀየሩ ፍቃዳቸው እንደሚሰረዝ ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤቱ ተናገረ…

ኢትዮጵያ በቅርቡ ህፃናትን በጉዲፈቻ ወደ ውጪ ሀገር መላክን በህግ መከልከሏ ይታወቃል፡፡

በጉዲፈቻ ወደ ውጪ ህፃናትን መላክ ልጆቹን ለማንነት ቀውስ፣ ለአካላዊና ሥነ-ልቦናዊ እንዲሁም ለማህበራዊ ግንኙነት ችግር አጋልጧቸዋል ተብሏል፡፡

...

ለህገ-ወጥ የሕፃናት ዝውውርም በር ከፍቷል በሚል ነበር የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሕፃናትን ወደ ውጪ አገር በጉዲፈቻ መላክን የሚከለክል አዋጅ ያፀደቀው፡፡

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲም ለሸገር እንደተናገረው ፍቃድ አውጥተው ወደ ውጪ ጉዲፈቻ ህፃናትን በመላክ ስራ ተሰማርተው የቆዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች 39 ናቸው፡፡

አሁን በቀደመ ስራቸው መቀጠል ስለማይችሉ አላማቸውን ቀይረው ወደ ሌላ ስራ ካልገቡ ፍቃዳቸውን እንደምሰርዝ አስጠንቅቄአቸዋለሁ ብሏል ኤጀንሲው፡፡

ድርጅቶቹ በሌላ ስራ ለመቀጠል እንደ አዲስ ተመዝግበው፣ የስራ መርሃ ግብርና ዝርዝር እቅድ ለኤጀንሲው በማቅረብ እንደ አዲስ ፍቃድ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

(ትዕግስት ዘሪሁን)

See More

የሳይንስ መረጃዎቻችን፣

በዚህ ሳምንት ከተሰሙ የሳይንስ መረጃዎች ግንባር ቀደሙ የፈረንሳይ ሳይንቲስቶች ይፋ ያደረጉት የጥናት ውጤት ነው፡፡ የጥናት ውጤቱ በፋብሪካ በከፍተኛ ሁኔታ የተቀነባበሩ ምግቦች ካንሰር አምጪ ናቸው ይላል፡፡ በ105 ሺ ሰዎች ላይ የተሰራው ይሄው ጥናት እንደሚለው ሰዎች በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን አብዝተው የሚመገቡ ከሆነ ለካንሰር የመጋለጣቸው እድል ይጨምራል፡፡

ውፍረት እና ሲጋራ ማጨስ ለካንሰር አጋላጭ ናቸው የሚለው የዓለም የጤና ድርጅት በፋብሪካ የተቀነባበረ ስጋን ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ለካንሰር አጋላጭ ነው ይለዋል፡፡...
ፈረንሳያዊያኑ ተመራማሪዎች አብዛኞቹ ሴቶች የሆኑበትን የጥናቱን ፍቃደኞች የአመጋገብ ሁኔታ ለ5 ዓመታት ተከታትለዋል፡፡ በዚህም መሰረት የጥናቱ ተሳታፊዎች የሚመገቡት በፋብሪካ የተቀነባበረ ምግብ መጠን በ10 በመቶ ሲጨምር በካንሰር የተያዙ ሰዎች ብዛት ደግሞ በ12 በመቶ ሲጨምር ታይቷል፡፡

“በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦች መመገብ አሁን ባለው ሁኔታ እየጨመረ ከመጣ በቀጣይ አስርት ዓመታት በካንሰር የመያዝ ሁኔታ እጅጉን ያንረዋል” የሚለው ይህ የጥናት ውጤት በብሪቲሽ ሜዲካል ጆርናል ላይ ታትሞ ወጥቷል፡፡

በዚህ ሳምንት የተሰማው ሌላው የሳይንስ መረጃችን ደግሞ እፅዋት በምድራችን ላይ ብቅ ስላለቡት ወቅት አዲስ መረጃ እነሆ ይለናል፡፡

ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከመሬት 4.5 ቢሊየን ዓመታት ዕድሜ ውስጥ፣ በመጀመሪያዎቹ 4 ቢሊየን ዓመታት ከማይክሮብ በስተቀር ምንም ዓይነት ሌላ ሕይወት አልነበረም፡፡ እናም በጥንታዊ እፅዋት ቅሪት ላይ በተደረገ ጥናት የመጀመሪያዎቹ እፅዋት በምድራችን ላይ ብቅ ያሉት የዛሬ 400 ሚሊየን ዓመታት ግድም እንደሆነ ነበር የሚታሰበው፡፡

Molecular Clock Method የተሰኘ አዲስ የምርምር ስልት በቀደሙት ስልቶች ላይ በመጠቀም በተደረገ አዲስ ጥናት ግን ሳይንቲስቶች እፅዋት በምድራችን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ብቅ ያሉበት ጊዜ በፊት ከሚታሰበው በ100 ሚሊየን ዓመታት የቀደመ መሆኑን ደርሰውበታል ነው የተባለው፡፡

በዚህ መሰረት Proceedings of the National Academy of Sciences በተባለው የምርምር መፅኄት ላይ የታተመው የምርምር ውጤት እንደሚለው እፅዋት በምድራችን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ብቅ ያሉት የዛሬ ግማሽ ቢሊየን ዓመታት ግድም ነው…

ለዓመታት ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የኳንተም ኮምፕዩተር እውን መሆን እየተቃረበ ነው ይለናል ቢቢሲ ይዞት የወጣው የሳይንስ መረጃ፡፡

ተመራማሪዎች ከሲልከን ፕሮግራም ሊደረግ የሚችል የኮምፕዩተር አብሰልሳይ (Processor) መፍጠር መቻላቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ የምርምር ቡድኑ በማይክሮዌቭ ሐይል በመጠቀም ባጣመሯቸው ኤሌክትሮኖች የሒሳብ ቀመር መስራት ችለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ያሉ ኮምፕዩተሮች በአዎ እና አይደለም ወይም በዜሮ እና አንድ ወይም (ቢትስ) ስሌታቸውን የሚቀምሩ ሲሆን ኳንተም ኮምፕየተሮች በበኩላቸው ክዩቢትስ በሚሰኙ መንታ የኳንተም ጥምረቶች አማካኝነት ነው ቀመራቸውን የሚሰሩት…

የኳንተም ኮምፕዩተር ሥርዓት በቀላሉ ከውጪ በሚፈጠር ተፅእኖ ሊረበሽ ይችላል የሚለው ዘገባው፣ ይህ ተፅእኖ የኳንተም ሥርዓቱ የተሳሳተ መልስ እንዲሰጥ ሊያደርገው እንዲሁም መላውን የኳንተም ኮምፕዩተር ስርዓት ሊንደው ይችላል፡፡

ስለዚህም ከኳንተም ስርዓቱ ውጪ የሚመጣን ተፅእኖ ለመመከት ተመራማሪዎች ተጨማሪ ክዩቢት እንደተጠቀሙ ተጠቅሷል፡፡

የምርምር ውጤቱ ኔቸር በተሰኘው ሥመጥር የሳይንስ ምርምር መፅኄት ላይ ታትሟል፡፡

See More
Image may contain: food
Image may contain: one or more people, grass, mountain, outdoor and nature

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሙሉ መመሪያ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባሳለፍነው አርብ ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል።

ክፍል አንድ፡ የተከለከሉ ተግባራት

...Continue Reading
It looks like you may be having problems playing this video. If so, please try restarting your browser.
Close
2.9K Views

በገና ደርዳሪው ዓለሙ አጋ ከመዓዛ ብሩ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ ወደ ኦፊሺያል የዩትዩብ ቻናላችን ጎራ ብላችሁ እንድታዳምጡ ጋብዘናል…

Alemu Aga on Chewata Eangda ,አለሙ አጋ - የጨዋታ እንግዳ Sheger 102.1 fm
youtube.com

እግር አልሰራ ሲል እጅ እግር ይሆናል…

ለማ ጅማ ገና የ3 ዓመት ጨቅላ ሳለ ነበር የእግሩ ነገር አልሆን ያለው፡፡ አላስቆም አላስኬድ አለው፡፡ በእጆቹ ተገልብጦ መሄድ ጀመረ፡፡ የ5 ልጆች አባት የሆነው እና አሁን በሚያገኛት ጡረታ የሚተዳደረው ለማ እያረፍኩም ቢሆን አንድ ጤነኛ ሰው በእግሩ የሚሄደውን ያህል እሄዳለሁ ይላል፡፡

ደረጃ እና ፎቅ መውጣት ቢፈትነኝም ቁልቁለት ግን የውሃ መንገድ ነው ለእኔ ይላል፡፡...
70 ደረጃን በ5 ደቂቃ እወርዳለሁ ባይ ነው - ለማ፡፡

የማይቻል ነገር የለም የሚለው ለማ ደስተኛ ነው፡፡ ተገልብጦ በእነዛ ጠንካራ እጆቹ በፍጥነት ሲሄድ ያዩ ሁሉ ይገረማሉ፡፡

እጆቹ ሁሉ ነገሮቹ ናቸው፡፡ ይሄድባቸዋል፤ ይበላባቸዋል…

በኢንጪኒ ወረዳ የአካል ጉዳተኞች ማህበር ሊቀመንበር ሆኖም ብዙዎችን አስተምሯል ይለናል ለማን ያነጋገረው ወንድሙ ኃይሉ፡፡

ለማ እንዲህ የጠነከርኩት በእጄ ስለሄድኩ ነው ይለናል፡፡

የለማን ነገር የሰማው ቼሻየር ለለማ ተሽከርካሪ ወንበር ሰጥቶታል…

ወደ ዩትዩብ ቻናላችን ጎራ ብላችሁ ሙሉውን ያዳምጡ

See More
Sheger Liyu Were, እግር ኣልሰራ ሲል እጅ እግር ይሆናል ፣ ሸገር ልዩ ወሬ ፤ በወንድሙ ሀይሉ #Sheger FM 102.1
youtube.com

መሪ ራስ አማን በላይ (1942-2010) - ሦስተኛ እና የመጨረሻ ክፍል

ተፈሪ ዓለሙ በ“ትዝታ ዘ አራዳ” መሰናዶው በያዝነው ዓመት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩንን ኢትዮጵያዊውን ምሁር መሪ ራስ አማን በላይን የዘከረበትን ሦስተኛ እና የመጨረሻ ክፍል
እነሆ ብለናል

Meri Rass Aman Belay - Part One - መሪ ራስ አማን በላይ ክፍል -፫(3) - ትዝታ ዘ አራዳ በተፈሪ አለሙ #Sheger FM 102.1
youtube.com

መንግስት ባለፉት አምስት አመታት ከገዛው ከ4 ሺህ በላይ መኪና ከሀገር ውስጥ አምራቾች የተረከበው ከ6 በመቶ አይበልጥም ተባለ፡፡

የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ለሸገር እንደተናገረው ባለፉት አምስት አመታት መንግስት ከ5.4 ቢሊዮን ብር በሆነ ወጭ 4 ሺህ 701 ተሽከርካሪዎችን ገዝቷል፡፡
ከመካከላቸውም 4 ሺህ 164 ቱን ከተለያዩ አለም አገራት አስገብቷል፡፡

...

በአገር ውስጥ መኪና ገጣጥመው ከሚሸጡ ፋብሪካዎች መንግስት በ5 አመት ውስጥ የገዛው የመኪና ቁጥር እጅግ ዝቅተኛ ነው የተባለ ሲሆን በ340 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር 537 መኪኖችን ብቻ ነው የገዛው፡፡

በአገልግሎቱ ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ጎጃም ታደለ ለሸገር እንደተናገሩት መንግስት ለሚገዛቸው መኪኖች የአገር ውስጥ አቅራቢዎች ድርሻ ዝቅተኛ የሆነው ባለባቸው የአቅም ችግር ምክንያት ነው ብለዋል፡፡

ለመንግስት መኪኖችን አቅርበዋል ከተባሉ የአገር ቤት ፋብሪካዎች መካከል መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪግ፣ ያንግ ፋም ሞተርስና በላይ አብ ሞተርስ ይገኙበታል፡፡

በዚህ በጀት አመትም መንግስት 639 ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ሒደት ላይ ነው የተባለ ሲሆን 4 መቶ ያህሉን ከአገር ውስጥ የመኪና አቅራቢዎች ለመግዛት ተሰናድቷል መባሉን ሰምተናል፡፡

(ትዕግስት ዘሪሁን)

See More

በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የወንጀል ተከሳሾች የጥብቅና አገልግሎት መስጠቱን ተናገረ፡፡

የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤቱ በ2010 ዓ/ም 6 ወራት በሁሉም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ባሉ የወንጀል ችሎቶች ለተከሰሱና ጠበቃ የማቆም አቅም ለሌላቸው 3526 ተከሳሾች ነው አገልግሎቱን የሰጠው፡፡

ጽ/ቤቱ ለተከሳሾች በጥብቅና ከመቆም በተጨማሪ በፍ/ቤት ክርክር የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በማዘጋጀት፣ በህግ ምክር በማድረግ ድጋፍ አድርጓልም ተብሏል፡፡

...

በወንጀል ተከሰው በራሳቸው ጠበቃ ለማቆም እና ለመከራከር የማይችሉ ተከሳሾች የክርክር ሰነድ በማዘጋጀት እና ለተከሳሾች በማረሚያ ቤት በመገኘት የህግ ድጋፍ ማድረጉን ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰምተናል፡፡

ጽ/ቤቱ በዚህ አመት በነፃ የጥብቅና አገልግሎት የሰጣቸው ተከሳሾች ካለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ሲመሳከርም ብልጫ ያለው ነው ተብሏል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ50 ሺ በላይ ለሚሆኑ ተከሳሾች የነፃ የህግ ድጋፍና የጥብቅና አገልግሎት መስጠቱ ተናግሯል፡፡

(ምህረት ስዩም)

See More

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ 11 ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች ታግደዋል ተብሎ በተለያዩ ሚዲያዎች የተላለፈው ዘገባ ሀሰት መሆኑን እወቁልኝ አለ፡፡

ኤጀንሲው በላከልን መግለጫ እንደተናገረው ማሪስቶፕስና ቼሻየር ፋውንዴሽንን ጨምሮ 11 ድርጅቶች በአዲስ አበባው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ መታገዳቸው በሚዲያ ተላልፏል፡፡

“ይህ ግን ሀሰት ነው፡፡ በጎ አድራጊ ድርጅቶችና ማህበራትን ፈቃድ የመስጠትና ጥፋት ሲገኝባቸውም የመዝጋት ስልጣኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ነው” ብለዋል፡፡

...

በመሆኑም ታግደዋል የተባሉት 11 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ስራቸውን እንደወትሮ እየከወኑ መሆኑን እወቁልኝ ብሏል ኤጀንሲው ፡፡

(ትዕግስት ዘሪሁን)

See More

የአለቃ ገብረሃና ነገር…

በመላው ኢትዮጵያ ታሪካቸውን ያልሰማ ማግኘት ይከብዳል፡፡ ስማቸው ሲጠቀስ ብዙዎች ቀልዶቻቸውን አስታውሰው ፈገግ ይላሉ፡፡ አለቃ ግን ሐገር የመሰከረላቸው ታላቅ ሊቅም ነበሩ…

ለመሆኑ አለቃ ገብረሃና ማናቸው ? ተፈሪ ዓለሙ በትዝታ ዘ አራዳ መሰናዶው የእኚህን ተወዳጅ ኢትዮጵያዊ ታሪክ ያስቃኘበትን ፕሮግራሙን የመጀመሪያ ክፍል ወደ ሸገር ኦፊሺያል የዩትዩብ ቻናል ጎራ ብላችሁ ታዳምጡ ዘንድ ጋብዘናል...

Aleqa gebrehana on tizta zearada አለቃ ገብረሃና -ትዝታ ዘ አራዳ በተፈሪ አለሙ, Sheger FM
youtube.com

በአዲስ አበባ ሴቶች የአስገድዶ መደፈር ጥቃት እንደሚደርስባቸው ይሰማል፡፡

በርዕሠ ከተማችን አዲስ አበባ ሴቶች የሚደፈሩባቸው አጋጣሚዎች ምን አይነቶች ናቸው ? ንጋቱ ሙሉ የሚከተለውን አዘጋጅቷል፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)

It looks like you may be having problems playing this video. If so, please try restarting your browser.
Close
9.6K Views

ጊታሪስት እና የሙዚቃ አቀናባሪ ሚካዔል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) በቅዳሜ ምሽት የለዛ ፕሮግራም ከአዘጋጁ ከብርሃኑ ድጋፌ ጋር ያደረገውን ቆይታ ያዳምጡ…

ሚካዔል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ከብርሃኑ ድጋፌ ጋር በለዛ ፕሮግራም - Miki Jano with Birhanu Digaffe On Leza Program - Sheger FM
youtube.com