Mehr von Prosperity Party - ብልፅግና auf Facebook anzeigen

Aktueller Beitrag der Seite
በአዲስ አበባ ከተማ ለብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉ...ት ለተከታታይ 11 ቀናት ሲሰጥ የነበረው የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ስልጠና በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አዳራሽ የስልጠናው የመዝጊያ ስነ ስርዓት ተከናወነ ።
በስልጠናው መዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ብልፅግና የሀሳብ ድህነት የሌለበት ፓርቲ ነው ፤ ብዙ የተጻፉና የተሰነዱ ሀሳቦች አሉት ፤ እነዚህን ሀሳቦች ወደ ተጨባጭ ተግባር ለማስገባት አመራሩ ከህዝቡ ጋር በመሆን በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንደሚገባው አንስተዋል ።
ብልፅግና የኢትዮጵያን ክብርና ህልውና የማይደራደር ፓርቲ መሆኑን እንዲሁም መደመርን መንገዳችን በማድረግ መዳረሻችንን ብልፅግና መሆኑን በማወቅ የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ እንዳለብን አንስተዋል ።
በተጨማሪም በአንድ ሀገር ውስጥ የህግ የበላይነትን የማስከበር ሁኔታ ለድርድር የሚቀርብ አለመሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የገለጹ ሲሆን አመራሩ ህግን የማስከበር ስራ ዋነኛ ተግባሩ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል። Mehr anzeigen
የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር አብይ አህመድ በመላ ሀገሪቱ በስልጠና ላይ ለቆዩ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮ...ች ማጠቃለያ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች
///////// ብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ///////////
// ብልፅግና የሀገርን ህልውናን ለመታደግ ድርብ ሀላፊነትን የወሰደ ፓርቲ ነው፤
// ኢህአዴግ በሞት አፋፍ ላይ የነበረ ድርጅት ሲሆን አዲስ ሀይል ፣አዲስ ጉልበት በመያዝ ራሱን እንደ አዲስ የፈጠረ ፓርቲ ነው፤
// ለውጡ ጥልቅ እና ፈጣን ነው፤
// በአንድ ሀገር ውስጥ ዴሞክራሲ ዕውን የሚሆነው የህግ የበላይነት ሲከበር ነው፤
// የህግ የበላይነትን የማስከበር ሁኔታ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም፤ህግ ማስከበር የመጀመሪያ ስራችን ዋና ተግባራችን ነው፤
// የትግራይ ህዝብ የብልፅግና ዋና ደጋፊ ነው፣ምንም እንኳ ይህንን ብልፅግናን ስሙ እንዲጠፋ የሚሰሩ ለውጥ የማይፈልጉ ሀይሎች ቢኖሩም፤ የትግራይን ህዝብ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የግድ ነው፡፡
// ህገ መንግስቱን በረጋና በሰከነ መንገድ፣በውይይትና በህገ መንግስታዊ አካሄድ ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ነው፤
// ብልፅግና የሀሳብ ድህነት የሌለበት ፓርቲ ነው፣ብዙ የተፃፉና የተሰነዱ ሀሳቦች አሉት፤እነዚህን ሀሳቦች ወደ ተጨባጭ ተግባር ማስገባት ያስፈልጋል
// ምርጫው በተያዘለት ጊዜ የሚካሄድ ነው የሚሆነው፤ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ እንዲሆን የሁሉም ሀላፊነት ነው የሚሆነው፣የህግ የበላይነት ማስከበርም ,
// ሀገራችን ኢትዮጵያ እውነተኛ ፌደራሊዝም የሚተገበርባት ሀገር እንድትሆን ብልፅግና አበክሮ ይስራል፤
// ለብልፅግና እውቀት ሲደመር እውነት እኩል ይሆናል ውጤት ነው፤ የሚመጣው ውጤት ደግሞ በጥራቱ የሚፈተሽ መሆን አለበት፤
// መደመር መነሻውንም መዳረሻውንም ሰው ላይ ያደረገ ዕሳቤ ነው፤
// መደመር መንገዳችን ብልፅግና ደግሞ መዳረሻችን ነው፡፡
መደመር መስመር መንገድ /Highway/ ነው፤በዚህ ጉዟችን ደግሞ የኢትዮጵያን ብልፅግና እናረጋግጣለን፤
// ብልፅግና ፓርቲ የክልልነት ጥያቄ እንዳይነሳ አይልም፤ዋናው ቁም ነገሩ ከህዝቡ ተጠቃሚነት አኳያ ነው መመዘን ያለበት፤ለዚህ ደግሞ ውይይት ክርክር ጥናት ያስፈልጋል፤
// ክልል በመፍጠር ሂደት ውስጥ ሀገር እንዳይፈርስ ቆም ብሎ ማሰብ እና ማጤን ለጋራ ተጠቃሚነት መስራት ያስፈልጋል፤
// ከውጭ ለምናገኘው ሀብት ብለን ሀገራዊ ክብራችንን አሳልፈን አንሰጥም፤
// ግድቡን የሌሎችንም ሀገራት ጥቅም በማይጋፋ መልኩ አጠናቀን ጥቅም ላይ እናውለዋልን፤ምንም እንኳ ቀደም ብለን ማጠናቀቅ ቢኖርብንም፤ስለዚህ በባለፈው ሳንቆጭ የያዝነውን ሳንለቅ ግድቡን አጠናቀን የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መስራት ያስፈልጋል፤ Mehr anzeigen
