ስዩም ተሾመ ስድ እና በጥላቻ የተሞሉ ጽሑፎች በሶሽል ሚዲያ ይጽፍ እንደነበር የአደባባይ ሚስጥር ነው። በዛ ምክንያት ለሚደርስበት አጸፋ ስድነት እና ጥላቻ መከላከል ራሱ ያቻለ ሌላ አድካሚ ስራ ነበር። እኔ በግሌ ስድነቱ እና ጥላቻው በዚሁ ሜዳ እየሞገትኩት ብቀጥል እመርጣለሁ። ሕግ የስዩምን አካሄድ እንደዛ ያየዋል ወይ የሚለውን ርእስ ወደ ጎን ትተን፣ ስዩም ከሞያ ስነምግባር እና ከሚሰራበት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም አንጻር ሲታይ እንኳ ስዩም ራሱ የሚደግፈው አይመስለኝም።